የDCPS የተማሪ – ወደ ምርቃት፣ የስራ-መስክ እና የኮሌጅ መመሪያ/Guide – ለተማሪዎች እና ቤተሰቦች ደረጃ-በደረጃ በምርቃት፣ በኮሌጅ እና በስራ-መስክ የመጓዣ-መንገዶች (career pathways) ላይ፣ መመሪያ የሚሰጥ፣ ለየግል-የተዘጋጀ ሰነድ ነው።
የ12ኛ ክፍል-ተማሪዎች፣ ‘መመሪያው/The Guide’ን – በበልግ/Fall ወቅት ውስጥ ያገኛሉ፤ በአንፃሩ-ደግሞ ከ9ኛ – 11ኛ ክፍል-ያሉ ተማሪዎች – ‘መመሪያው/The Guide’ን በፀደይ/Spring ወቅት ውስጥ ያገኛሉ።
ይህ ገጽ፤ በመመሪያችሁ/guide ውስጥ ያለውን መረጃ፣ በተሻለ-ሁኔታ ለመረዳት የሚያስችል የመረጃ-ምንጮችን አካቷል።
ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሏችሁ፣ በትምህርት ቤታችሁ የሚገኘውን የሠራተኛ-አባልን ከማነጋገር ወደኋላ-አትበሉ ወይም በdcpsguide@k12.dc.gov ኢሜል አድርጉ።
የምርቃት ክፍሉ/The Graduation Section፤ ወደ ከፍተኛ-ደረጃ ትምህርት ቤት ምርቃት ያላችሁን አስደሳች-ጉዞ፣ ይዘረዝራል! በዚህ ክፍል/section ውስጥ፣ በእያንዳንዱ የትምህርት-ዓይነት ዙሪያ – የሚፈለጉትን ሴሚስተሮች/semestersን ዝርዝር-ሆኖ የተቀመጠውን መረጃ፣ ከማህበረሰብ አገልግሎት ሰዓታት – አዲስና-ማሻሻያ/update ጋር ሆኖ – ታገኛላችሁ።
በተጨማሪም፤ ወደ ምርቃት ባላችሁ ጉዞ “በትክክለኛው-መንገድ ላይ/on-track” ወይም “ከመንገዱ-የወጣችሁ/off-track” መሆንና-አለመሆናችሁንም ታያላችሁ። ይህ ሁኔታ፣ የምርቃት መስፈርቶችን ለማሟላት – የሚያስፈልጉትን ቁልፍ ኮርሶች አልፋችሁም-ከሆነም ወይም ካልሆነ፣ ወይም-ደግሞ በአሁኑ-ጊዜ ተመዝግባችሁ በመሆንና-አለመሆን ላይ – ወይም የማህበረሰብ አገልግሎት መስፈርቶችን ያሟላችሁ ከሆነ – በዚህ-ላይ የተመሰረተ ነው።
ስለ ምርቃት ሁኔታዎች-ላይ፣ በማህበረሰብ ሰዓታት፣ ወይም በትራንስክሪፕት ላይ – ማንኛውም ጥያቄዎች ካሏችሁ፣ እርዳታ-ለማግኘት ካውንስለራችሁን ከማነጋገር ወደኋላ-አትበሉ።
በመመሪያው ውስጥ የሚገኝው የትምህርት ውጤት ማስረጃ (transcript)፣ ህጋዊ (official) የትምህርት ውጤት ማስረጃ (transcript) ነው?
የለም፣ አይደለም። ህጋዊ (official) የትምህርት ውጤት ማስረጃ (transcript)፣ በትምህርት ቤት ኃላፊ (አስተዳዳሪ ወይም ካውንስለር) ህጋዊ ፊርማ የተፈረመበት መሆን አለበት። አብዛኛዎቹ ተቀባይ የሆኑ ተቋማት፣ የትምህርት ውጤት ማስረጃው ህጋዊነት (official) ሆኖ እንዲቆጠር የታሽገ እንዲሆን ይጠይቃሉ።
እኔ በትክክለኛ-መንገድ (on track) እንደሆንኩኝ እያወኩኝ፣ ለምንድነው የምርቃት ገጽ – በትክክለኛው-መንገድ ላይ ያልሆነ (off track) በሚለው-ስር በመዘርዘር-ያስቀመጠኝ?
የበልግ መመሪያ (The Fall Guide)፤ እስከ ሴፕቴምበር (September) ድረስ ያላችሁን ሁኔታ እና የውጤት-ደረጃዎችን የሚያንጸባርቅ እና የፀደይ መመሪያ (Spring Guide) ደግሞ እስከ ፌብሩዋሪ (February) ድረስ ያላችሁን ሁኔታ እና የውጤት-ደረጃዎችን ያንጸባርቃል። የእናንተን ካውንስለር በመጎብኘት (በመመሪያ/Guide ገጽ 1 ላይ የተዘረዘሩትን) – አሁን-ያላችሁ ክፍሎች/classes፣ በትክክለኛው-መንገድ ላይ እና ከመንገዱ ውጪ/on- or off-track የመሆን ሁኔታችሁን ላይ ያለውን ተጽዕኖ ምን-እንደሆነ ለማየት-ጎብኙ።
የትምህርት ውጤት ማስረጃዬ (transcript) በቂ ሰዓታትን እንዳገኘው ሲናገር፣ ለምንድነው የምርቃት ገጹ – የማህበረሰብ አገልግሎቴ ያልተጠናቀቀ አድርጎ-የዘረዘረው?
በአንዳንድ-አጋጣሚዎች፣ የምርቃት ገጹ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት ሰዓታትን በትክክል-ላያሰላው ይችል-ይሆናል። የምርቃት ገጻችሁ ወይም የእናንተ የትምህርት ውጤት-ማስረጃ (transcript) ትክክል-ላይሆን ይችላል ብላችሁ የምታስቡ-ከሆነ፣ ካውንስለራችሁን አግታችሁ-አነጋግሩ።
የትምህርት ውጤት ማስረጃዬ (transcript) ወይም የደረጃ ውጤቴ የተዛባ ከሆነስ ምን ይሆናል?
በመጀመሪያ፤ ከትምህርት ቤት ካውንስለራችሁን ማነጋገር አለባችሁ። እባካችሁ፣ በተጨማሪም – በDCPSguide@k12.dc.gov ላይ ኢሜል ላኩ።
የኮሌጅ ክፍል/The College Section፤ ከቤተሰባችሁ ጋር – የኮሊሌጅ መግቢያ/college admission ሂደትን ለመዳሰስ፣ ተመራጭ-የሆነው የመረጃ-ምንጫችሁ ነው። ማመልከቻዎችን – ከማዘጋጀት እና ከማስገባት ጀምሮ፣ እስከ ምዝገባ እና ከዚያም-በላይ በሆነ-ሁኔታ፤ በእያንዳንዱ የመጓዣ እርምጃ ውስጥ – ለመምራት እዚህ-እንገኛለን። እንዲሁም፤ የእናንተ ‘GPA’፣ የፈተና የውጤት-ደረጃዎች፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ-ያሉ እንቅስቃሴዎች/extracurricular activities እና የኮርስ ምርጫዎች፤ ወደ ተለያዩ ኮሌጆች የመግባት-ዕድሎቻችሁ ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ግልጽ-ግንዛቤን ታገኛላችሁ።
እነዚህ ገፆች፤ የየግል-የሆነ ድጋፍ-መስጫዎች/personalized recommendationsን ለ”Smart Colleges”—በአካዳሚክ መገለጫችሁ/academic profile ላይ መሠረት-አድርጎ በላቀ-ደረጃ ልትሰሩባቸው በምትችሉባቸው ትምህርት ቤቶች —እና ለእናንተ የሲኒየር ዓመት/senior year እና ወደ ኮሌጅ ለሚደረገው ጉዞ፣ ሙሉ-በሙሉ ዝግጁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ የሚወሰዱ የእርምጃዎች ፍኖተ-ካርታን – ያቀርባል።
ግልጽነት-ባለው ሁኔታ እና በልበ-ሙሉነት፣ ወደ ኮሌጅ የመጓዣ-መንገዳችሁ ለመግባት – ተዘጋጁ!
የእኔን የናቪያንስ (Naviance) ገጼን – ማግኘት የምችለው የት ነው፤ እና እንዴት ነው መግባት (login ማድረግ) የምችለው?
ኮሌጆቹ ተመርጠው የነበሩት እንዴት ነበር?
የስማርት ኮሌጅ ዝርዝር/The Smart College List፤ ጠንካራ-የሆነ የተማሪ ስኬት ሬከርድ-ያላቸውን እና በከፍተኛ-ደረጃ ትምህርት ቤታችሁ ውስጥ ካሉት ተማሪዎች መካከል – ታዋቂ-የሆኑን፤ የኮሌጆች ዝርዝር – ናሙና ነው። የተዘረዘሩት ኮሌጆች፣ ለማንኛውም ይሄ-ነው ለተባለ ተማሪ፤ ሁሉንም አጠቃላይ የአማራጭ-ዝርዝርን – የሚወክል አይደለም። ኮሌጆችን እንዴት መፈለግ እንደሚቻል የበለጠ ለማወቅ፣ የናቪያንስ (Naviance) ቪዲዮአችንን በhttp://bit.ly/naviancesupermatch. ላይ – ተመልከቱ።
የስራ-መስክ ክፍል/The Career Section፤ ከእናንተ ልዩ-የሆነ ፍላጎቶች እና ምኞቶች ጋር የሚጣጣሙትን፣ የስራ-መስክ የመጓዣ-መንገዶች (career pathways)ን ለመፈተሽ፣ እንደ መግቢያ-በር ሆኖ ያገለግላል!
ለድህረ ሁለተኛ-ደረጃ/Postsecondary የዳሰሳ-ጥናታችሁ በሰጣችሁት ምላሾች ላይ መሠረት-አድርጎ፣ በትምህርት-ደረጃ ከተከፋፈሉት አማካኝ-የሆነ ደሞዝ ጋር – ሦስት ለየግል-የተዘጋጀ የስራ-መስክ የመጓዣ-መንገዶች (career pathways)ን – ያሳዩዋችኋል። በተጨማሪም፤ በእነዚህ መስኮች ውስጥ ስኬትን ለማግኘት የሚረዳችሁን፣ ሃሳብ-የቀረበባቸውን የ2- እና የ4-ዓመት የኮሌጅ ፕሮግራሞችን ታገኛላችሁ።
የስራ-መስክ ሂደታችሁን ለማፋጠን ወይም ለተጨማሪ ትምህርትን ለመከታተል የምትፈልጉ-ከሆነ፤ ይህ ክፍል/section – በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን እንድትወስኑ እና ለወደፊት ስኬታችሁ በራስ የመተማመን እርምጃዎችን እንድትወስዱ የሚያግዙ ጠቃሚ-የሆኑ ግንዛቤዎችን ይሰጣል።
የስራ-መስክ ስብስቦች (clusters)፣ እንዴት ነው የተመረጡት?
የስራ-መስክ ስብስቦች (clusters) የተማሪዎች – ለድኅረ-ሁለተኛ ደረጃ የዳሰሳ-ጥናት/postsecondary survey በሰጡት ምላሶች ላይ መሠረት ያደረጉ-ናቸው። ተማሪው – የዳሰሳ-ጥናቱን ካላጠናቀቀ፣ ሦስት የዲሲ አካባቢ ከፍተኛ የደሞዝ/ከፍተኛ-ተፈላጊነት ያላቸው የስራ-መስክ ስብስቦች (clusters)ን እንዲወጡና እንዲታዩ አድርጓል: የ‘Business Administration’፣ የ‘Information Technology (IT)’፣ እና የ‘Health Sciences’።
የደሞዝ እና የስራ-ክፍያ/salary መረጃዎች፣ እንዴት ነው የተወሰኑት?
ለዲሲ የሜትሮ አካባቢ፣ የደሞዝ/wage እና የስራ-ክፍያ/salary መረጃዎች የተወሰዱት፣ ከ‘Bureau of Labor and Statistics (BLS)’ ነበር።
ስለ ተጨማሪ የስራ-መስኮች እና ኮሌጆች መማር የምችለው የት ነው?
ስለኮሌጆች እና የስራ-መስኮች፣ የበለጠ በስፋት ለማወቅ፤ ናቪያንስ (Naviance) አንዱ ግሩም የሆነ ቦታ ነው፡፡ በclever.com ውስጥ፣ የትምህርት ቤታችሁን ናቪያንስ/Naviance ገጽን – መጎብኘት ትችላላችሁ።
የሚቀጥሉት እርምጃዎች ክፍል/The Next Steps Section፤ በእናንተ የምርቃት፣ የኮሌጅ እና የስራ-መስክ ግቦች ላይ ባላችሁ ውጤታማነት ላይ ለመርዳት – ተጨማሪ ተግባራት ላይ ትኩረቱን ያንጸባርቃል። በእነዚህ እርምጃዎች ላይ – የድኅረ-ሁለተኛ ደረጃ ግቦቻችን ለማሳካት፣ በትክክለኛው-መንገድ ላይ/on track ለመቆየት – በእነዚህ እርምጃዎች ላይ – ከትምህርት ቤታችሁ እና ቤተሰባችሁ ጋር መስራት!
ተርም / TERM | ትርጓሜ / DEFINITION |
ምርቃት፣ ኮሌጅ፣ እና የስራ-መስክ የድርጊት-እርምጃዎች | ምርቃትን ለማረጋገጥ እና የድኅረ ሁለተኛ ደረጃ ግባቸውን ለማሳካት፤ የተማሪውን በየየግል-የተዘጋጀውን የሚወሰዱትን የሚቀጥለውን እርምጃዎችን – ይወክላል። |
የድኅረ ሁለተኛ-ደረጃ የመጓዣ-መንገድ ግብ / Postsecondary Pathway Goal | በድህረ ሁለተኛ ደረጃ የዳሰሳ-ጥናታቸው ውስጥ – በናቪያንስ/Naviance ውስጥ የተያዘው፣ የምርቃት-በኋላ – በተማሪው የተመረጠው ግብ። ግቡ፤ ከሚከተሉት – ማንኛውን በቅንብር ሊያካትት ይችላል: – አፕሪየንትስሺፕ/Apprenticeship: በአንድ የተወሰነ ዘርፍ ውስጥ፣ የ‘journeyman’s license’ን ለማግኘት፤ ክፍያ-ባለው፣ በስራ-ቦታ ላይ በመገኘት የስራ-ስስልጠና ፕሮግራም። – የስራ-መስክ ትምህርት: ልዩ-የሆነ የምስክር ወረቀት ወይም ፍቃድ ለማግኘት፤ አስፈላጊ ችሎታዎችን የሚያስተምር – የአጭር-ጊዜ የስልጠና ፕሮግራም። – ቅጥር/Employment: የከፍተኛ-ደረጃ ዲፕሎማ ወይም ‘GED’ን ከጨረሱ-በኋላ፣ ወዲያውኑ በከፍተኛ ደሞዝ/ከፍተኛ-ተፈላጊነት ባላቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ስራዎችን መፈለግ። – ውትድርና/Military: በU.S. military ውስጥ – በ‘Air Force’፣ ‘Army’፣ ‘Coast Guard’፣ ‘Marines’፣ ‘Navy’፣ እና ‘National Guard’ ውስጥ በመሳተፍ-አማካኝነት የሚገኙ የስራ-መስኮች። – የ2-ዓመት ዲግሪ: ቢያንስ 60 የክሬዲት ሰዓቶችን ማጠናቀቅን የሚፈልግ – የ‘Associate’s degree’። ይህ ዲግሪ፣ በተለመደ-ሁኔታ – በኮሙኒቲ ኮሌጅ ውስጥ የሚጠናቀቅ-ነው። |
የቀለም-ትምህርት ግብ / Academic Goal | ከአካዳሚ ጋር የተያያዘ ግብ፤ በተማሪው በድህረ ሁለተኛ ደረጃ/postsecondary የዳሰሳ-ጥናታቸው ውስጥ በተፃፈው-መሠረት። |
በመመሪያ/Guide ውስጥ ያለው – የተማሪው መረጃ የተገኘው ከየት ነው?
መረጃ ዝርዝሩ (data) የወጣው፣ ከ‘Aspen’፣ ‘Naviance’፣ እና ከድህረ-ሁለተኛ ደረጃ የዳሰሳ ጥናቶች ነው።
በመመሪያ/Guide ውስጥ ያለው-የመረጃ ስብስብ (data)፣ ለምን ጊዜውን-የጠበቀ/up-to-date – አይደለም?
መመሪያው/The guide፤ የእናንተን የቀለም-ትምህርት ሂደትን እስከ ሴፕቴምበር (September) 2024 ድረስ ያለውን ይንጸባርቃል። አንዳንድ ዝርዝሮች ሊለወጡ-የሚችሉ ሆነው እያለ፣ ይህ መረጃ – በመኖሪያ-ቤት ውስጥ እና በትምህርት ቤት ውስጥ – ስለ አካዳሚክ ግቦች እና የወደፊት እቅድ-አወጣጥ፣ ውይይቶች እንደ-መጀመሪያ ሆኖ ያገለግላል። የተማሪያችሁን የቅርብ-ጊዜ – በትምህርት-ገበታ ላይ መገኘት/attendanceን፣ የውጤት-ደረጃዎች/gradesን፣ እና ክሬዲቶች/creditsን ለመመልከት፤ የወላጅ እና ተማሪ ፖርታል/Parent and Student Portalን፣ በhttps://dcps.dc.gov/page/parent-portal ላይ ጎብኙ።
የመመሪያውን የዲጂታል ስሪት (digital version)፣ ከየት ነው የማገኘው?
የዲጂታል ስሪቶቹ (digital versions) በአስፐን (Aspen) ላይ ይገኛል። ተማሪዎች፣ አስፐን/Aspenን – በክሌቨር (Clever) አካውንታቸው አማካኝነት – ማግኘት ይችላሉ። የወላጅ እና ተማሪ ፖርታል (Parent & Student Portal)ን ለማግኘት እና ለመዳሰስ እንዴት-እንደሚቻል – ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፤ በhttps://dcps.dc.gov/page/parent-portal ላይ ጎብኙ።
በየስንት ጊዜው ነው መመሪያውን የማገኘው?
መመሪያው/The Guide፤ በበልግ (fall) ወቅት ላይ ለ12ኛ ክፍል-ተማሪዎች፣ እና በፀደይ (spring) ሴሚስተር ወቅት-ላይ ደግሞ ከ9 -11 ክፍል ተማሪዎች – መገኘት-የሚችል ይሆናል።
መመሪያው በምን ቋንቋዎች ነው የሚገኘው?
መመሪያው፤ በአማርኛ፣ በቻይኒኛ፣ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በስፓኒሽ እና ቬትናም ቋንቋዎች ይገኛል። እያንዳንዱ ወላጅ፣ የእንግሊዘኛ ቅጂውንም ያገኛሉ።
በመመሪያዬ ላይ የተዛባ-መረጃ ቢኖር፣ ማድረግ ያለብኝ ምንድን ነው?
እባክዎን፣ በDCPSguide@k12.dc.gov ኢሜል ያድርጉ እና ካውንስለራችሁን አነጋግሩ። የትምህርት ቤት ካውንስለራችሁ፣ በይበልጥ – ወቅታዊ የሆነ መረጃ ይኖራቸዋል።
መመሪያዬን፣ እነማን ማግኘት ይችላሉ?
የእናንተ ወላጅ/አሳዳጊ፣ ካውንስለሮች፣ የኮሌጅ እና የስራ-መስክ አስተባባሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ እና የትምህርት ቤት አስተዳደሮች፣ በአስፐን/Aspen ላይ የእናንተን መመሪያ/Guide መመልከት-ይችላሉ። በተጨማሪም፤ የDCPS ተማሪዎችን የሚያገለግሉ በትምህርት ቤት ላይ መሠረት-ያደረጉ አጋር-የትብብር ድርጅቶች እና የመረጃ ስብስቦችን በጥበቃ-ለመያዝ ቃል-ኪዳን የፈረሙ የማግኘት-አቅም የሚኖራቸው ሲሆን፤ ነገር-ግን ይህ-ለተወሰኑ ለሚያገለግሏቸው ተማሪዎች ብቻ ይሆናል።
ሰለ መመሪያው ወይም ስለእኔ የድኅረ-ሁለተኛ ደረጃ የሽግግር የመጓዣ-መንገድ/postsecondary pathway፤ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉኝ ማንን ነው ማነጋገር ያለብኝ?
በመመሪያ የመጀመሪያ-ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን፣ ካውንስለር ወይም የኮሌጅና የስራ-መስክ አስተባባሪውን ማነጋገር ይኖርባችኋል። ስለመመሪያው አጠቃላይ ጥያቄዎች፣ ወደ DCPSguide@k12.dc.gov ሊላኩ-ይችላሉ።